የሰሜን ወሎ ሲቪልሰርስ እና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ

የደመወዝ ማሻሻያው ትርጉም ኖሮት እንዲቀጥልና የሸቀጦች የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር መከላከል የሁሉም ሀላፊነት መሆኑ ተገለፀ

የድህረ ገጹ እይታ ብዛት.

+

ከወረዳወች የተላከ መረጃ ብዛት

.

በድህረ ገጹ

.

Image Services

የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ

"የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ የ2017 ዓ.ም የዞኑን መምሪያዎች የለውጥ ስራዎች ምዘና አካሄደ። መስከረም 7/2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን ) የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ የሰው ሃብት ልማት መምሪያ እንደሚታወቀው ወደ ጎን የሚያስተዳድራቸውን ተቋማት የለውጥ ስራወች የመደበኛ ተግባር ማሳላጫ ሆነው እንዲተገበሩ በተቀመጠው አሰራር ወጥ የሆነ የድጋፍና ክትትል ስርአት ዘርግቶ እየሰራ የቆየ መሆኑን የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ሃላፊ ወ/ሪት ሙሉ አዲሴ የገለፁ ሲሆን በዚህም ተቋማት በሁሉም ተግባራት ከጊዜ ወደ ጊዜ ያላቸው የአፈጻጸም ደረጃ እየተሻሻለ የመጣበት ሁኔታ እንዳለ ሃላፊዋ ጨምረው ገልፀዋል ። "



የሰሜን ወሎ ሲቪልሰርስ እና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ወልዲያ

About Our Consulting Firm
ለህዝባችን ዘላቂ ልማት እና ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚተጋ ሲቪል ሰርቫንት ለመገንባት የሪፎርም ሥራውን ከፍ ባለ ቁርጠኝነት ለመፈፀም እንሰራለን። ክቡር አቶ አረጋ ከበደ

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የ2017ዓ.ም በጀት አመት የማጠቃለያ መመዘኛ ነጥብ:-

እንደ መምሪያችን በማዘጋጀት ከመምሪያው ማናጅመንት አባላትና ከሪፎርም ድጋፍና ክትትል ቡድን ጋር የጋራ በማድረግ ቡድኖቹን በማቀናጀት መምሪያወቹን የአካል ምዘና እንዲያደርጉ መምሪያው ተልኮ የሰጠ ሲሆን በዚሁ መሰረት ኮሚቴው የአካል ምዘናውን ጀምሯል ።

ባለን ክትትልም:-

ባለን ክትትልም ሁሉም ባይባልም የአብዛሀኛው ተቋም ሰራተኛ የተሰጠውን ሙያዊ ተግባርና ሀላፊነት በአግባቡ እየተወጣ መሆንኑ አረጋግጠናል። ወቅታዊ ተግዳሮት ሳይበግራቸው ቀድሞ ከነበረው በተሻለ ሁኔታ ስራቸውን የሚያከናውኑ መኖራቸውን መዛኝ ቡድኑ የአረጋገጠ ሲሆን አንዳንድ ወጣ ገባ የሚሉም ተቋማት ከቀጣይ አኳያ የድጋፍና ክትትል አግባቡን አጠናክረን በማስቀጠል በቁርጠኝነት እንሰራለን በማለት ሃላፊዋ ተናግረዋል።

መረጃ አያያዝ ከወረዳ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት

የግዳን ወረዳ፣የላስታ ወረዳ፣ ሲ/ሰ ሪከርድና ማህደር በዲጂታል መልኩ መደራጀቱ ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ እንዲሁም ቀልጣፋ ሁኔታን የፈጠረ ነው።

መረጃ አያያዝ ከከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት

ላሊበላ ከተማ አስተዳደር ፣የሃራ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ፡የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ሙሉ በሙሉ መረጃቸውን በጥራት አስገብተዋል።

ቀዳሚ
ቀጣይ

የደመወዝ ማሻሻያው ትርጉም ኖሮት እንዲቀጥልና የሸቀጦች የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር መከላከል የሁሉም ሀላፊነት መሆኑ ተገለፀ።

NWCIV:01-11-2025 15:25pm

ወልድያ፦ ጥቅምት 11/2018 ዓ. ም (ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን) የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ሃገራዊ የደመወዝ ጭማሬውን አስመልክቶ በወጡ ደንቦችና መመሪያዎች ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ትውውቅ አካሄደ። የሰሜን ወሎ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ከድር ሙስጠፋ እንደገለፁት የተደረገው የደመወዝ ማሻሻያ የመንግስት ሰራተኛውን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ለማጎልበት ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል። ማሻሻያው የአገልግሎት አሰጣጡን በጥራት በውጤታማነትና በቅልጥፍና ያለምንም አድሎ በመፈፀም ለላቀ የህዝብ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችልም ነው ብለዋል። የደመወዝ ማሻሻያው ትርጉም ኖሮት እንዲቀጥልና የሸቀጦች የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር መከላከል የሁሉም አካል ሀላፊነት መሆኑን አሳስበዋል። የመምሪያው ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉ አድሴ እንዳሉት ተቋሙ ለሀገረ መንግስት ግንባታው ውጤታማነት ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል ብለው በመጣንባቸው ጊዜያቶች በየደረጃው ያሉ አመራርና ባለሙያዎች በተለያዩ ዘርፎች የአገልጋይነት ስሜት ተላብሰው ህዝቡን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፤ አሁንም በማገልገል ላይ ናቸው ብለዋል። ለአመራሩና ለመንግስት ሰራተኛው የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረው የኑሮ ማሻሻያና ጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች መልስ ያገኙበት ነው ያሉት ሀላፊዋ ሀገራዊ የደመወዝ ጭማሪውን መሰረት ያደረገባቸው ሀሳቦችና መመሪያዎች ዙሪያ ውይይት በማድረግ ግልፅነት መፍጠር ተችሏል ብለዋል። በየደረጃው ያሉ የሰው ሀይሎች ያለማንም ጎትጓች ሀገራዊ የሪፎርም ትግበራው እውን እንዲሆን ሁሉም የተጣለበትን ሀላፊነት በአግባቡ መወጣት አለበት በማለት ሀላፊዋ አሳስበዋል። የዞኑ ገንዘብ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ጀነቴ አያሌው እንደገለፁት የደመወዝ ጭማሪው ያስፈለገበት ምክንያት የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት፣ የስራ ተነሳሽነትን ለመፍጠርና ህገወጥነትን ለመቀነስ ታስቦ መሆኑን ገልፀዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ውይይቱ በወጡ መመሪያዎችና ደንቦች መሰረት ለመስራት የሚያስችል ነው ብለው የደመወዝ ጭማሪውን ተከትሎ የሚደረጉ የሸቀጦችና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ የዋጋ ጭማሪዎችን ከንግድና ከህግ አካላት ጋር በጋራ በመስራት ህገወጦችን መከላከል ይገባል ብለዋል።

ወቅቱ የሚጠይቀውን የዘመነ አገልግሎት ለመስጠት የሰው ሀይሉ ራሱን በቴክኖሎጂ እንዲያለማና ለመጪው የዲጂታላይዜሽን ዘመን ራሱን ማሰልጠን እንዳለበት የሰሜን ወሎ

NWCIV:01-11-2025 15:22pm

ወቅቱ የሚጠይቀውን የዘመነ አገልግሎት ለመስጠት የሰው ሀይሉ ራሱን በቴክኖሎጂ እንዲያለማና ለመጪው የዲጂታላይዜሽን ዘመን ራሱን ማሰልጠን እንዳለበት የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ አስታወቀ፡፡ ጥቅምት 11/2018 ዓ/ም(ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን ) የሰ/ወ/ዞ/ሲ/ሰ/የሰ/ሀ/ል መምሪያ የ2018 ዓ.ም በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት ተግባር አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል፡፡ በመጀመርያው ሩብ አመት ሊሰሩ ከታቀዱት ውስጥ በጥንካሬ የፈጸምናቸውን ጠብቀን በማስቀጠል በድክመት አቅደን ያልፈጸምናቸውን ለይተን የቀጣይ የእቅድ አካል አድርገን በፍጥነት በማረም ለውጥ ማምጣት አለብን ሲሉ የመምሪያው ሃላፊ ወይዘሮ ሙሉ አዲሴ ተናግረዋል፡፡ ሃላፊዋ በሩብ አመቱ ሊከናወኑ ከታቀዱት ተግባራት ውስጥ በርካታ ተግባራት በተሻለ አፈጻጸም የተከናወኑ ሲሆን በተለይ ከለውጥ ተግባራት ጋር በተያያዘ ወደ ጎን የምናስተዳድራቸው ተቋማት በየደረጃው ያለ ሲቪል ሰርቪስ ተቋም በተቀመጠው አሰራር በተደረገው ወጥ የሆነ ድጋፍና ክትትል እነዚህን ተግባራት የመደበኛ ተግባር ማሳለጫ መሆናቸውን አምኖ በመተግበርና በማስተግበር በኩል የተሰራው ስራ የመጣው የአመለካከት ለውጥ በማህበራዊ በኢኮኖሚና በመልካም አስተዳደር ለተገኘው ስኬት የጎላ አስተዋጽኦ የተመዘገበበት ነው ብለዋል፡፡ የሰው ሀይሉ የመጣውን ሀገራዊ ሪፎርም በውል ተረድቶ የመፈጸም አቅሙም እንዲያድግ የሰው ሀይሉ በእውቀት እንዲሻሻልና እንዲለማ እየተሰጡ ያሉ የትምህርት እድሎች አበረታች ናቸው ስራ የሚሰራው በሰው ሀይል ስለሆነ በቀጣይም አማራጮችን በማስፋት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ሲሉም ወይዘሮ ሙሉ ተናግረዋል፡፡ ወቅቱ የሚጠይቀውን የዘመነ አገልግሎት ለመስጠት የሰው ሀይሉ ራሱን በቴክኖሎጂ እንዲያለማና ለመጪው የዲጂታላይዜሽን ዘመን ራሱን እንዲያሰለጥን በየደረጃው የተሰሩት ስራወች ውጤት የተመዘገበባቸው መሆናቸውና ይህንን ተደራሽ በማድረግ በኩል ተግባሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ሃላፊዋ ገልፀዋል፡፡ የሰው ሀይል ስምሪቱ የሜሪት ህጉን ጠብቆ እንዲፈጸም በተደረገው ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር መሻሻሎች መኖራቸውና ቀጣይም የቅደመ መከላከልና የመደበኛ ኢንስፔክሽን ተግባራት ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸው፣ እንደ ሀገር የተደረገው ደመወዝ ማሻሻያ በየደረጃው ያለውን የሰው ሀይል ወደስራ የሚያስገባና መነሳሳትን የፈጠረ በመሆኑ ይህን ምቹ አጋጣሚ ተጠቅሞ በሁሉም ዘርፍ የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ መትጋት እንደሚያስፈልግ በየደረጃው በሁሉም ዘርፍ የመፈጸም አቅምን በማሳደግ ደህንነቱ የተጠበቀ ቀልጣፍና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት ወቅቱ የሚፈልገውን የተገልጋይን ርካታ ማረጋገጥ ከመምሪያው እና ከስሩ በሚገኙ አካላቶች የሚጠበቅ ተግባር መሆኑ በውይይቱ የተነሱ ሃሳቦች ናቸው፡፡ በውይይቱ የወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ሲ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት ሀላፊወች፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር ሲ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት ቡድን መሪወች፣ የዞኑ ሲ/ሰ/የሰ/ሀ/ል መምሪያ ጠቅላላ ሰራተኞች እና አጋር አካላት ተገኝተዋል፡፡ በመጨረሻም በመጀመርያው ሩብ ዓመት ወረዳዎች ከተማ አስተዳደሮች እና የመምሪያው ሰራተኞች ማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የሰው ሀይሉ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዲገባ ስራ ቆጥሮ ሰጥቶ በመቀበል ሂደትና የተሻለ የሰራን በማበረታታት የተገልጋዩን ፍላጎት ማርካት እንደሚገባ ተገለፀ፡

NWCIV:01-11-2025 15:00pm

ወልድያ ፦ ጥቅምት 13/2017 ዓ/ም( ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን) የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ በ2017 ዓ.ም በጀት አመት በለውጥ አተገባበር ስራ ወደ ጎን ከሚያስተዳድራቸው ተቋማት በበጀት አመቱ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን የእውቅናና የማበረታቻ ስርአት ፕሮግራምና የ2018ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት የለውጥ ተግባር አፈጻጸም የዞኑ ስራ አስፈጻሚ፣ የዞኑ ጠቅላላ አመራር እና የዞኑ ቡድን ሸ በተገኙበት ገመገመ፡፡ በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አራጌ ይመር ባለፉት ስኬቶች ለተመዘገቡት የልማት የመልካም አስተደደር እንዲሁም ሌሎች ዘርፎች ላይ ለተገኙት ስኬቶች እነዚህ የተግባር ማሳለጫ ቁልፎች ያበረከቱት አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከቀጣይ አኳያም ተቋማዊ ጥንካሬ ለመፍጠር በሁሉም ዘርፍ እስከታችኛው መዋቅር ያሉ አደረጃጀቶችን ተጠቅሞ ወደ ስራ እንዲገቡ አቅዶ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡ አጠቃላይ የሰው ሀይሉ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዲገባ ስራ ቆጥሮ ሰጥቶ በመቀበል ሂደትና የተሻሉትን በማበረታት አሰራርን ጠብቆ በማስቀጠል ወቅቱ የሚፈልገውን ጠንካራ የድጋፍና ክትትል እስከ-ተጠያቂነት ስርአት መዘርጋት አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡ የሰ/ወ/ዞ/ሲ/ሰ/የሰ/ሀ/ል መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ሙሉ አዲሴ የለውጥ ስራወች የመደበኛ ተግባር ማሳለጫ ሆነው እንዲተገበሩ በ2018ዓ.ም በ1ኛ ሩብ አመት በተደረገው ድጋፍና ክትትል የተሰሩት ስራወች ውጤት የተመዘገበባቸው እና አብዛሀኛወቹ ተቋማት ወደ ተቀራራቢ አፈጻጸም ያመጡ ናቸው ብለዋል። በቀጣይ በጀት አመትም የበለጠ እንዲተገበሩ ከተቀመጠው አሰራር ከፍ ባለ ደረጃ ወጥና ጠንካራ የሆነ የክትትልና የድጋፍ ስርአት በመዘርጋት የተቋማትን የመፈጸም አቅም ማሳደግ ላይ ተግተን እንሰራለን ሲሉ ወ/ሮ ሙሉ ገልፀዋል፡፡ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ዞናችን ያለበትን ሁኔታ ስንመለከት በበርካታ ዘርፎች ህዝብን አርክተናል ማለት አይቻልም ባለን ክትትልም ይህንኑ አረጋግጠናል እነዚህን መሰረታዊ ክፍተቶች አርመን ቀጣይ ወደ ተሻለ የአፈጻጸም ቁመና ለመግባት ከወቅቱ ጋር የሚሄድ ዘመናዊ አሰራርን ለመከተል የተጀማመሩ ስራወችን ይበልጥ አጠናክረን በማስቀጠል ችግሮቹን ለመሻገር እንጥራለንም ብለዋል። ከተሳታፊዎችም ከመንግስት ሰራተኛው አኳያ የነበረውን የኑሮ ማሻሻያ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ እንደ መንግስት በተጠና፣ በተደራጀና በፈጠነ መልኩ ምላሽ ተሰጥቷል። ይህንን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የሰው ሀይሉ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዲገባ በየደረጃው ያለው አመራር በስራ ማረጋገጥ አለበት የሀገራዊ ሪፎርም አተገባበር ስራወች መሬት እንዲነኩ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ በየደረጃው ያለውን የሰው ሀይል በእውቀት፣ በቴክኖሎጂ እንዲለማና እንዲበለጽግ እንደመምሪያችን የተለያዩ ስልጠናወችን እየሰጠን ነው፤ እንደ-ሀገር የሰው ሀይሉ በኮደርስ እንዲሰለጥን የመጡት እድሎችም የሚደነቁ ሆነው ሌሎች ተጨማሪ አማራጮችን በማስፋትም ሰው ሀይል ልማት ላይ መሰራት እንዳለበት በውይይቱ የተነሱ ሃሳቦች ናቸው፡፡ በመጨረሻም ሲቪል ሰርቪስ መምሪያው ከለውጥ ተግባራት ጋር በተያያዘ ወደ ጎን የሚያስተዳድራቸውን ተቋማት ባደረገው አመታዊ ምዘና ከተካሄደባቸው 33 የዞን ተቋማት በሪፎርም(በለውጥ) ስራ በተቋማት አያያዝ እና አሰራር መመሪያ ተመዝነው ብልጫ ላመጡ የዞን መምሪያዎች የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡

ለአስተያየት እና ተያያዥ ጉዳዮች ቀጣዩን ፎርም ይጠቀሙ.

እኛን ለማግኘት


ኢሜል:

northwollociv@gmail.com

ስልክ:

+251-333361405

አድራሻ:

ወልዲያ

ኢትዮጵያ