የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች ማረጋገጫ (Verification) መመሪያ
11-05-2026 12:15pm 📄 የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች ማረጋገጫ (Verification) መመሪያ
📌ይህ ሰነድ የማረጋገጫ ሂደቱ ስልታዊ እና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ እንዲከናወን የሚረዱ ሶስት ዋና ዋና ክፍሎችን ይዟል።
📋 ክፍል 1፡ የግድ መሟላት ያለባቸው ሰነዶች (11 ዓይነቶች)
ለእያንዳንዱ ሰራተኛ ሊሟሉ የሚገባቸው መሰረታዊ የሰው ኃይል መረጃዎች፦
📌ብሄራዊ መታወቂያ፡ ከተመዘገበበት ስልክ ቁጥር ጋር።
📌የቢሮ መታወቂያ፡ ወቅታዊ የሆነ።
📌የቅጥር ደብዳቤ፡ የመጀመሪያ ቅጥር ሰነድ።
📌የዝውውር ሰነድ፡ ከሌላ መሥሪያ ቤት የመጡ ከሆነ።
📌የደረጃ እድገት፡ የተሰጡ የደረጃ እድገት ደብዳቤዎች።
📌የአገልግሎት ማራዘሚያ፡ ጡረታ ወጥተው ለሚሰሩ ብቻ።
📌የትምህርት ማስረጃዎች፡ ሁሉም የትምህርት ደረጃዎች።
📌የጡረታ ፎርም፡ የተሞላ የጡረታ መረጃ።
📌የስራ ልምድ፡ የቀድሞ የስራ ልምድ ማስረጃዎች።
📌የሹመት ደብዳቤ፡ ተሿሚ ለሆኑ አመራሮች።
📌የድልድል/ምደባ ደብዳቤ፡ አዲስ ድልድል ተደርጎ ከሆነ።
💍 ክፍል 2፡ ተጨማሪ የማህበራዊ ሁኔታ ሰነዶች
📌የጋብቻ ሰርተፍኬት
📌የልጆች የልደት ሰርተፍኬት (ልጆች ካሉ)
⚙️ ክፍል 3፡ የአሰራር ቅደም ተከተልና መመሪያዎች
✍ሂደቱ ያለምንም መስተጓጎል እንዲሄድ ተቋማት የሚከተሉትን ተግባራት ማከናወን ይኖርባቸዋል፦
📌መርሃ-ግብር ማዘጋጀት፡ በቀን ለአንድ መረጃ ሰብሳቢ 7 ሰራተኞችን በማደራጀት ቀኑን አስቀድሞ ማሳወቅ።
📌የአካል መገኘት፡ በወሊድ፣ በህመም ወይም በአመት እረፍት ላይ ያሉ ሰራተኞች በአካል ቀርበው መመዝገብ አለባቸው።
📌የሰው ኃይል መመደብ፡ ስራውን የሚከታተል፣ ጥንቃቄ ያለውና የIT እውቀት ያለው ኃላፊ መመደብ።
📌 መረጃዎችን - በጊዜ፣ በጥራትና በማደራጀት የዲጅታል ሲቪል ሰርቪስ ግንባታን ለማሳካት የድርሻቸውን እንወጣ። መልዕክታችን ነው።
የአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ
ይህ መረጃ 41 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----
ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇 👇 👇 ሚዲያወች በመጫን Share..
