"Please wait"
እባክዎ በትዕግስት ይጠብቁ የኢንተርኔትዎ ዳካማ መሆን ነው!

Home About Us Main point Service Job Vacancy Comment

የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ

06-05-2026 14:33pm

ሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ እና ሰዉ ሐብት ልማት መምሪያ ለመንግስት ሰራተኛዉ በፐርሶኔል መረጃ ማጥራትና ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ።
ሚያዚያ-28/2018ዓ.ም(ወልድያ
የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ እና ሰዉ ሐብት ልማት መምሪያ በዞኑ ለሚገኙ ጠቅላላ የመንግስት ሰራተኞች ስለ ፐርሶኔል መረጃ ማጥራት እና ማረጋገጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩም የመምሪያዉ ኃላፊ ወ/ሪት ሙሉ አዲሴ ስለ ፐርሶኔል መረጃ ማጥራትና ማረጋገጥ አላማ እና ከመንግስት ሰራተኛዉ ጋር ያለዉን ግንኙነት በተመለከተ የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበዋል።
በሰነዱም አንድ መደብ ለአንድ ባለሙያ በሚል መርህ የስራ መደቦችን እና በምን ያህል የሰዉ ኃይል እንደተሸፈኑ ለመለየት እንደሚያስችል ተገልጿል።
ሌላዉ ሰራተኛዉ የያዘዉ መደብና የትምህርት ዝግጅትንም መለየት ስለሚቻል ስራና ተዛማጅነትንም ለማወቅ እንደሚረዳም ተመላክቷል።
እንዲሁም የሰራተኛዉ ፕሮፋይል ሲያዝ ከፋይዳ መታወቂያዉ ጋር ስለሚያያዝ የሰራተኛዉን ፕሮፋይል በቀላሉ የትም ሁኖ አክሰስ ማድረግ እንደሚቻል እና ማጭበርበርን ማስቀረት እንደሚቻልም በሰነዱ ላይ ተገልጿል።
ስለዚህ የመንግስት ሰራተኛዉ የተሟላ ቋሚ መረጃ እንዲኖረዉ የተሟላ መረጃ መስጠት እና ለስራዉ ተባባሪ መሆን እንደሚገባዉም የመምሪያዉ ኃላፊ ወ/ሪት ሙሉ አዲሴ አሳስበዋል።

loading

loading

loading

ይህ መረጃ 150 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----

   ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇    👇    👇    ሚዲያወች በመጫን Share..

Comment Form

Designed And Developed By ➜ YONAS WODAY HAILU