✅
02-05-2026 15:09pm👉ቀልጣፋና ውጤታማ የመንግስት አገልግሎት እንዲኖር ለማድረግ ለሲቪል ሰርቫንቱ የስልጠና መርሃ ግብሮችን በመንደፍ ክህሎታቸውን፣ እውቀታቸውን እና ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ ያደርጋል፣ ሙያዊ እድገት እና ውጤታማ የመንግስት አስተዳደርን እንዲረጋገጥ ይሰራል፤
👉የክልሉን እቅድ ለማሳካት የሰው ኃይል ፍላጎትን በመተንተንና የመጭውን ፍላጎት በመተንበይ ሲቪል ሰርቪሱ በቂ እና የሰለጠነ የሰው ሃይል መሟላቱን ያረጋግጣል፣ ለተግባራዊነቱም ይሰራል፤
👉ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን የሲቪል ሰርቪስ አገልጋይነትን ለማጠናከር፣ ተነሳሽነቶችን ለማሳደግ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ እና የመንግስት አቀፍ ስትራቴጂዎችን ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል፤
👉ቴክኖሎጅን በመጠቀም ከተገልጋይ እና ከሰራተኛ እርካታ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን በመሰብሰብ እና በመተንተን ፖሊሲ ለመቅረፅ እና አሰራሮችን ለማሻሻል የሚያስችሉ ጥናት ያደርጋል፣ በግኝቱ መሠረት የማሻሻያ ሃሳቦች በመቅረፅ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
👉የሲቪል ሰርቪሱን ባህርያት ከተቋማት ፖሊሲ፣ ራዕይ፣ ዕሴቶች እና ግቦች ጋር እንዲጣጣም፣ ሰራተኞች ምቾት ተሰምቷቸው ስራን በብቃት እንዲሰሩና ሕዝብን በቅንነት እንዲያገለግሉ የሚያደርግ ምቹ የሥራ ቦታና የስራ አውድ እንዲፈጠር ይሠራል፡፡
ይህ መረጃ 15 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----
ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇 👇 👇 ሚዲያወች በመጫን Share..
