✅
02-05-2026 15:09pm👉የክልሉ መንግሥት ሠራተኞች ሥነ ምግባር ለማሻሻል የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
👉ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ እና የቅሬታ ማስተናገጃ ሥርዓት መዘርጋታቸውን እና ሥራ ላይ ማዋላቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣ ጉድለት ሲያጋጥም የእርምት እርምጃ ይወስዳል፣ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
👉የመንግሥት ሠራተኛ የጡረታ ዕድሜው ሞልቶ ነገር ግን በሚሰራበት ተቋም ለተጨማሪ ጊዜ እንዲያገለግል የተቋም ሃላፊ ጥያቄ ሲያቀርብ በህጉ መሰረት ውሳኔ ይሰጣል፤
👉ልዩ የሥራ ባህሪ ወይም የሥራ ክብደት ያላቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ላይ ተመስርቶ ልዩ ቅጥር እና ጥቅማጥቅም እንዲፈቀድ ጥያቄ ሲቀርብለት ጉዳዩን በጥልቀት መርምሮ ለክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፤
👉ውድድርን መሰረት ያደረገ ነፃ፣ ገለልተኛ፣ አካታችነትን ያረጋገጠ እና የክልሉን ብዝሀነት የሚያስተናግድ የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፤
ይህ መረጃ 2 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----
ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇 👇 👇 ሚዲያወች በመጫን Share..
