✅
02-05-2026 15:08pm👉በሲቪል ሰርቪስ ዘመናዊ የተሟላ ሰብአዊ ሀብት አመራር እንዲኖር በሠራተኞች ላይ የሚታዩ የአቅም ክፍተቶችን በጥናት ይለያል፣ በትምህርትና ስልጠና ያበቃል፣ የሰው ሀብት ልማቱን በተማከለ መልኩ ለመምራት የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊ እንዲሆን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ ይወስዳል፤
👉የሲቪል ሰርቫንቱን የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ሥልጠና የሚፈፀምበትን የአሰራር መመሪያ በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ስራ ላይ ያውላል፣ ይከታተላል፣
👉የሲቪል ሰርቪሱን አቅም ለመገንባት አስፈላጊ የሆኑ የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት እንዲሁም የብቃት ምዘና ማዕከላት እንዲቋቋሙ ለክልሉ መንግሥት ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ሥራ ላይ ያውላል፣ ይደግፋል፣ ያስተዳድራል፣
👉የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ በተመለከተ ጥናት ያደርጋል፣ ህዝባዊ መድረኮችን እና ወርክ ሾፖችን ያዘጋጃል፣ ውጤታማነቱን ያረጋግጣል፤
ይህ መረጃ 4 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----
ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇 👇 👇 ሚዲያወች በመጫን Share..
