✅
02-05-2026 15:07pm👉በክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ተቋማት የመንግሥት ሰራተኞች የሥራ አፈፃፀም ምዘና ሥርዓት ይዘረጋል፣ የመንግሥት ሰራተኞችን ብቃትና ውጤታማነት በየጊዜው ይገመግማል፣ ይመዝናል፣ እንዲመዘኑ ያደርጋል፣ የመንግሥት ሰራተኞች ብቃትና ውጤታማነት የሚገነባበትን ሥልት ይነድፋል፣ ሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፤
👉ለክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ተቋማት የመንግሥት ሠራተኞች የቅጥር፣ የምደባ፣ የዝውውር፣ የደረጃ እድገት አሰራር ፍትሃዊ፣ ግልጽ እና ብቃትን መሰረት ያደረገ እንዲሆን ያደርጋል፣ ያረጋግጣል፣ ሕግንና መርህን ተከትሎ እንዲፈፀም ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣ የስምሪት ጉድለት ሲፈጸም የእርምት እርምጃ ይወስዳል፣ያስወስዳል፤
👉በክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ውስጥ በመንግሥት ሠራተኞች የሚቀርቡ ይግባኞች በአስተዳደር ፍርድ ቤቱ አማካኝነት መርምሮና አጣርቶ በፍሬ ነገር ደረጃ ውሳኔ ይሰጣል፤
👉በሁሉም ተቋማት ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓት እንዲዘረጋ በማድረግ የክልሉን የመንግሥት ሠራተኞች ዝርዝር መረጃ መዝግቦ ይይዛል፣ ስታቲስቲካዊ መረጃዎችን ያጠናቅራል፤
ይህ መረጃ 2 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----
ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇 👇 👇 ሚዲያወች በመጫን Share..
