"Please wait"
እባክዎ በትዕግስት ይጠብቁ የኢንተርኔትዎ ዳካማ መሆን ነው!

Home About Us Main point Service Job Vacancy Comment

አቦሀይ ጋራ

22-04-2026 08:42am

አቦሀይ ጋራ ከባህር ጠለል በላይ እስከ ከ4 ሽህ ሜትር በላይ ከፍታ ይገኛል፡፡ ይህ ተራራ በውስጡ ከጀበራ ተክል ጀምሮ በርካታ እፅዋትና ብርቅየዋ ቀይ ቀበሮን ይዟል፡፡ ከነዚህ ሌላ ተራራው የኢትዮጵያ ህዋ ሳይንስ የምልከታ ስፍራ አድርጎ መርጦታል ፤ የምልከታ ማዕከሉም ከሀገሪቱ የህዋ ምርምር ጣቢያዎች ጋር እኩል ውጤት የሚታይበት በመሆኑ ለቀጣይ የሀገሪቱ የምልከታ ተግባርን ያቃልላል፡፡ ይህን የምልከታ ማዕከል የባህርዳር ፣ ጎንደር ፣ መቀሌና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር ስራ እንዲሰሩበት ከአቶ ተፈራ ዋልዋ ተረክበዋል፡፡ (ግዳን ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት)
የአፍታ ጉብኝት

በከፍታው ከኢትዮጵያ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ከአፍሪካ ደግሞ በ19 ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ከባህር ወለል በላይ 4260 ሜትር ከፍ ብሎ ይታል፡፡ ይህ ቦታ አቡነ ዮሴፍ ተራራ ነው፡፡
ባሕርዳር፡ሐምሌ 06/2010 ዓ/ም (አብመድ) አቡነ ዮሴፍ ተራራ ከላል ይበላ በስተ ሰሜን ምስራቅ የሚገኝ ተፈጥሮ የተጠበበችበት ድንቅ ስፍራ ነው፡፡ ወደ ስፍራው ካቀኑ ከሰማይ ጠቀሱ ተራራ ላይ ሆነው ዙሪያ ገባ የሚገኙ ድንቅ የመልከዓ ምድር ገጽታዎችንም ይመለከታሉ፡፡ብዙዎች ጎብኚዎችም የሰሜን ወሎ ጌጥ ሲሉ መስክረውለታል፡፡

አቡነ ዮሴፍ ከኢትዮጵያ በከፍታው 6ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ከአፍሪካ ደግሞ በ19 ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ከባህር ወለል በላይ 4260 ሜትር የሚገኘው ይህ ከፍተኛ ቦታ ከአካባቢው መልከዓ ምድር ደግሞ በ1909 ሜትር ከፍ ያለ ነው፡፡
አቡነ ዮሴፍ ተራራን ከሌሎች ተራሮች ልዩ የሚያደርጉት ገጽታዎችም አሉት፡፡ ተራራው በኢትዮጵያ ካሉ ትልልቅ ተራሮች በተለየ ሌሎች የመስህብ ስፍራዎች እና ቅርሶች በአካባቢው ይገኛሉ፡፡

ይምርሃነ ክርስቶስ፣ ጀመዱ ማርያም፣ ገነተ ማርያም፣ አሸተን ማርያምና ሌሎች ከአለት የተፈለፈሉ አብያተ ክርስቲያናት በአካባቢው ከሚገኙ የጎብኚዎች መዳረሻዎች ይጠቀሳሉ፡፡
የእንግሊዙ የከርሰ ምድር ተመራማሪ ክራውፎርድ “የጨረቃ ተራራ” ተብሎ በጥንቶቹ ግሪኮችና አረቦች የሚታወቀው ጀበል ኤል-ካማር ይህ ተራራ እንደሆነ ያስረዳል።
የጨረቃ ተራራ (ጀበል ኤል ካማር) በኋላም ለምድር ወገብ (ኢኩዌተር) ስሙን የለገሰ ድንቅ ተራራ ነው።

የተፈጥሮ ቅርስ በሆነው በዚህ ተራራ ላይ በተደረገ ጥናት የ43 አይነት አጥቢ እንስሳት መኖሪያ መሆኑ ተረጋግጧል፤221 አይነት ወፎችም ጎጇቸውን ቀልሰው ይኖሩበታል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙት ጭላዳ ዝንጀሮ እና ቀይ ቀበሮዎችም በዚሁ ቦታ ይገኛሉ ።
አቡነ ዮሴፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የአዕዋፍ መኖሪያ ስፍራዎች አንዱ እንደሆነም በጥናት ተረጋግጧል፤ በወፍ ሃብቱም ሁለተኛ ነው።
አካባቢውን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ሰዎች ስፍራው የተመቸ ነው፤ ለጎብኝዎችም ምቹ ማረፊያ አለው፡፡

ከሁሉም በላይ ግን የአካባቢው ማህበረሰብ የእንግዳ አቀባበል የቱሪስት መዳረሻው ቦታውን ደግመው እንዲጎበኙት የማድረግ ሃይል አለው፡፡

በምስጋናው ብርሃኔ (አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን)

loading

ይህ መረጃ 200 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----

   ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇    👇    👇    ሚዲያወች በመጫን Share..

Comment Form

Designed And Developed By ➜ YONAS WODAY HAILU