የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አራጌ ይመር ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
21-04-2026 20:30pmየሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አራጌ ይመር ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን )
የመልእክቱ ሙሉ ቃል
እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ!
ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ እንኳን ለዘንድሮዉ የገና በዓል በሠላም አደረሳችሁ ! አደረሰን! እያልኩ መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ ።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በታላላቅ ሀገራዊ ስኬቶች ታጅባ፣ የማንሰራራት ዘመን ጉዞዋን እያጠናከረች በምትገኝበት ምዕራፍ ላይ የምናከብረዉ የዘንድሮዉ የገና በዓል ፣ የአብሮነትና የመተሳሰብ እሴቶቻችንን በማጠናከር ፣በመደመር እሳቤ ተሳስረን፣ ለአዳዲስ ሀገራዊ ብስራቶች ፣በጋራ ለመትጋት መነሳሳትን የምንፈጥርበት ነዉ።
የገና በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት አንዱ ነዉ።
የገና በዓል ከሃይማኖታዊ ትዉፊቶቹ እና አስተምህሮቶቹ ባሻገር ፣ የመልካም ምኞት መግለጫ ስጦታዎችን በመለዋወጥ ፣ ፍቅርንና ትብብርን ለማደስ መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር ነዉ።
በዓሉ ማህበራዊ እሴቶችን የሚያነቃቃ፣ የወንድማማችነት/የእህትማማችነት መንፈስን የሚያድስና በአዲስ መንፈስ ለአዲስ ስኬት መነሳሳትን የሚያጎናጽፍ ነዉ።
በዓሉን ስናከብር ብሩህ ተስፋንና አሻጋሪ ህልምን ሰንቀን ፣ የአብሮነትና የመደጋገፍ እሴቶችን አልቀን ፣ ለጋራ ሠላምና ዕድገት በጋራ ለመትጋት ዝግጁነታችንን ከፍ በማድረግ መሆን ይኖርበታል።
ለሰሜን ወሎ ዞን ህዝብ የገና በዓል ልዩ ያደርገዋል ምክንያቱም ከመላው አለም የተወጣጡ ዜጎች እና ከሀገሪቱ ክፍል ተነስተው ገናን በላሊበላ እያከበሩ ስለሚገኙ ለዞኑ ህዝብ ትልቅ በዓል ነው።
መልካም የገና በዓል !
አመሠግናለሁ !
ይህ መረጃ 106 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----
ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇 👇 👇 ሚዲያወች በመጫን Share..
