"Please wait"
እባክዎ በትዕግስት ይጠብቁ የኢንተርኔትዎ ዳካማ መሆን ነው!

Home About Us Main point Service Job Vacancy Comment

ሁለተኛ ዙር የሰሜን ወሎ ዞን መንግስት ሰራተኛ ትምህርት ማስሪጃ የማጣራት ስራ ሊጀመር ነው ። ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን )

20-04-2026 08:57am

ሁለተኛ ዙር የሰሜን ወሎ ዞን መንግስት ሰራተኛ ትምህርት ማስሪጃ የማጣራት ስራ ሊጀመር ነው ።
ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን )
ሁለተኛ ዙር የመንግስት ሰራተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ስራ ሊጀመር መሆኑን የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ሃላፊ ወ/ሪት ሙሉ አዲሴ ገለፁ።
የመምሪያ ሃላፊዋ እንደገለፁት በየደረጃው ያሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት እንደ-ሀገር ከተቀመጡ ፖሊሲወች አንዱ በየደረጃው ያለውን አመራርና መ/ሰራተኛ የትምህርት ማስረጃ ማጣራት ስራ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ተናግረዋል ።
የዜጎች አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ብቃት ባላቸው ሰራተኞች አገልግሎት ለመስጠት ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ማጣራት ስራ የተጀመረው አንዱ የሪፎርም አካል ነው ብለዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ ሰው ሃብትወ ልማት መምሪያ ሃላፊ ወ/ሪት ሙሉ አዲሴ እንደተናገሩት የሀሰተኛ የትምህርት መረጃ የማጣራት ስራው በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።

loading

ይህ መረጃ 86 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----

   ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇    👇    👇    ሚዲያወች በመጫን Share..

Comment Form

Designed And Developed By ➜ YONAS WODAY HAILU